ሚኒስቴሩ ከሰብአዊ ድጋፍ በዘለል ተጋላጭ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስልቶች ላይ በማተኮር ከ ከአጋር አካላት ጋር ይሠራል – ክብርት ሁሪያ አሊ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሲርላና የበጎ አድራጎት ድርጅት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በመገኘት ለ 440 የሚጠጉ አባቶቻቸውን በተለያየ ምክንያት ላጡ ልጆችና እናቶች የማዕድ ማጋራት አድርጓል።

በሚኒስቴሩ የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በማዕድ ማጋራቱ ወቅት እንደተናገሩት ሚኒስቴሩ ፈጣን የሰብዓዊ ምላሾችን ለሚፈልጉ ዜጎች ድጋፎችን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በማድረስ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን ድጋፉን ዘላቂና አስተማማኝ ወደ ሆኑ አማራጮች መቀየር ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልፀዋል። ሚኒስቴሩ የሴቶችን፣ የህጻናትን፣ የአረጋውያንን እና የአካል ጉዳተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ በማረጋገጥ፣ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት አስተማማኝ አጋርነት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ለዚህም ከሰብአዊ ድጋፍ በዘለል ተጋላጭ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ ስልቶች ላይ በማተኮር ከ ከአጋር አካላት ጋር እንደሚሠራ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የተርክዬ ኤምባሲ ለተለያዩ የማህበራዊ ተግዳሮቶች ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች የተደረገውን መሰረታዊ የምግብ እርዳታ ድጋፍ ስላበረከተ አመስግነው ይህ ድጋፍ በኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጫና ውስጥ ላሉ ወገኖች አብሮነታችንን ለማሳየትና ትብብራችንን የሚያጠናክር ነው ሲሉ ገልፀዋል። የሲርላና በጎ አድራጎት መስራችና ስራአስኪያጅ ኡስታዝ ኑሩ ተርኪ በበኩላቸው የተደረገው ድጋፍ ወቅቱን ያማከለና የሚመሰገን መሆኑን ጠቅሰው ድጋፉን ላመጣው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴሮን አመስግነው በቀጣይም ከሌሎች አጋር ድርጆቶች ጋር ሚደረገው ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል ።

Please follow and like us: