Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 477 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 477 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 6 ዙር በረራ የተመለሱት 1 ሺህ 392 ወንዶች እና 85 ሴቶች ሲሆን ከተመላሾች መካከል 171 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 62 ሺህ 68 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል። ሚኒስቴሩ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል። መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋምም በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። በተለያዩ ጊዜያትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
Please follow and like us:
