የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የወንዶች ተሳትፎ ጉልህ አስተዎፅኦ እንዳለው ተገለጸ

ለስርአተ-ፆታ እኩልነት የወንዶችን በምልዓት የማሳተፍ ብሔራዊ ስትራቴጂ ዝግጅት ላይ ግብዓት ለማሰባሰብ ያለመ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎በመርሀ-ግብሩ ላይ የሴቶችና ህጻናት ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን የስርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የወንዶች ተሳትፎ ጉልህ አስተዎፅኦ እንዳለው ገልፀዋል። ‎ኢትዮጵያ በሴቶች ውሳኔ ሰጪነት ላይ በተሻለ መልኩ እየሰራች መሆኑ የተረጋገጠ ሁኔታ ላይ ብትሆንም :: ‎ሴቶች በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደ ሀገር የተቀመጡ ግቦችን በሚፈለገው መልኩ ለማሳካት ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ ‎ስትራቴጂው ሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እንዲሁም ፆታን መሠረት አድረገው የሚፈፀሙ ጥቃቶችንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከልና በማስቆም ረገድ ወንዶች በጎ ሚናቸውን እንዲወጡ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ሲሉ ተናግረዋል።

‎‎ስለ ሴቶች እኩልነት ስናነሳ ከጀርባ ሆነው በተሟላ መንገድ የሴቶችን ስራ ይዘው በተሻለ መልኩ የሚሰሩ ወንዶች መኖራቸውን ጠቅሰው የሚዘጋጀው ስትራቴጂ አበርክቷቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያስችላል ብለዋል። ‎የወንዶችን አጋርነት ለማሳደግ እንዲያስችል የተዘጋጀው የስትራቴጂ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊዎች ያላቸውን ልምድና የሌሎች ሀገራትንም ተሞክሮ መነሻ በማድረግ ሊያሰሩ የሚችሉ ጠቃሚ ግብዓቶችን ሰጥተውበታል። ‎በመርሀ-ግብሩ ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር፣ ከአፋር፣ ከትግራይ፣ ከአማራ፣ ከኦሮሚያ፣ ከጋምቤላ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከሀረሪ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንዲሁም ከፌደራል እና ከልማት አጋር የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል። > የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር – Ministry of Women and Social Affairs: 🖼 Photo

Please follow and like us: