Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የምገባ ማዕከላትን ለማጠናከር ተቋማት በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ተጠቆመ።
ይህ የተገለፀው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአዲስ አበባ ምገባ ኤጀንሲ የመመገቢያ ቁሳቁሶችንና አልባሳትን ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ነው
በዚሁ ወቅት የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የዜጎችን ማህበራዊ ፍትህ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መንግስት ከጀመራቸው ሰው ተኮር ተግባራት መካከል በመሆናቸው ማዕከላቱን ለማጠናከር ተቋማት በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።ጠንካራ የሆነ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋት ዜጎች ራሳቸውን በዘላቂነት በማቋቋም እራሳቸውን ብሎም ሀገራቸውን በኢኮኖሚው መስክ እንዲያግዙ ያስችላል ብለዋል፡፡ ዛሬ የተደረገው ድጋፍ ይህንኑ በከተማ አስተዳደሩ የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ በመቀጠል በአዲስአበባ ከተማ የሚገኙ የምገባ ማዕከላትም የዜጎችን ማህበራዊ ፍትህ እና ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ብሎም ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ተጋላጭ ለሆኑ የህበረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ እንደሚያስችል ጠቅሰዋል።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱም በተለያዩ ጊዜያት የዜጎችን ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ ያለሙ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም በበጋና ክረምት የሚከናወኑ የበጎ ፈቃድ ስራዎች ፤-የቤት ዕድሳት፣ ማዕድ ማጋራት እና ሌሎች መሰል ተግባራትን ተቋማዊ በሆነ መልኩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራባቸዉ የበርካቶችን ሸክም ያቀለሉ ተግባራትን በስፋት ማከናወኑን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
Please follow and like us:
