ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፋቸው ለምን አስፈለገ?

‎ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት መሳተፋቸው በዋናነት ከታች የተዘረዘሩትን ዋና ዋና ጉዳዮች ለመመለስ ያግዛል፡፡ እነዚህም ፦

‎‎• ወጣቶች በግጭቶችና አለመግባባቶች የበለጠ ተጎጂ በመሆናቸውና ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱና ሰላም እንዲሰፍን ወጣቶች ጉልህ ሚናና ድርሻ ስላላቸው፤
‎‎• ወጣቶች ለለውጥ ያላቸው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ አዳዲስ አስተሳሰቦችን እና አመለካከቶች በምክክር ሂደቶች ለማስተናገድ ቅርብ በመሆናቸው፤
‎‎• ወጣቶች በኢትዮጵያ የስነ-ህዝብ ምጣኔ ውስጥ ከአንድ ሶስተኛ በላይ ቁጥር ያላቸውና የእምቅ አቅም ባለቤት በመሆናቸው በጉዳዩ ላይ ዋነኛ ከዋኝ እንዲሆኑ ስለሚያስችላቸው፤
‎‎• ወጣቶች ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው እና ስለነገው የሀገራቸው ጉዳይ ባለቤት በመሆናቸው፤
‎‎• በወጣቶች ጥያቄና በጋራ በሚደረስባቸው ስምምነቶች የነገ ሀገር ስለምትፀና የሚሉት በዋነኝነት የሚጠቁሱ ናቸው፡፡
‎
‎በመሆኑም ወጣቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይ በንቃት እንዲሳተፉና በጎ ሚናቸውን እንዲያበረክቱ በስፉት ይጠበቅባቸዋል፡፡
‎
‎ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

Please follow and like us: