Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ወጣቱ ትውልድ ከአረጋውያን ልምድና እውቀት በመቅሰም ለማህበረሰብ ለውጥ ብሎም ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ እድገት የድርሻውን መወጣት አለበት – ክብርት ሁሪያ አሊ
የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋውያን በህይወት ዘመናቸው የቀሰሙትን እውቀት፣ ክህሎት እና ተሞክሮ ለወጣቱ ትውልድ ማስተላለፍ እንዲችሉ ያለመ የትውልድ ቅብብሎሽ መድረክ አካሂዷል።
በዕለቱ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ እንደገለፁት አረጋውያን በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በኢኮኖሚ ልማት፣ በፖለቲካ አመራር፣ በግጭት አፈታት እና በሀገር አንድነት አጠባበቅ ላይ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል ። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአረጋውያንን መብቶች ከማስከበር ባለፈ በልምድ ያካበቱትን እምቅ እውቀት ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ድልድይ ሆነው እንዲያገለግሉ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ወጣቱ ትውልድ ከአረጋውያን ልምድና እውቀት በመቅሰም ለማህበረሰብ ለውጥ ብሎም ለዘላቂ ሰላምና ሀገራዊ እድገት የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል። ወጣቱ ትውልድ ተንቀሳቃሽ ቤተ-መፅሐፍት ከሆኑት አረጋውያን ጥበብንና እውቀትን በመቅሰም በፈጠራና አዳዲስ ቴክኖሎጂን በማበልፀግና የትውልድ ክፍተትን በማጥበብ የበለፀገችና አካታች፣ ዘላቂ ሰላም እና እድገት የሰፈነባት ኢትዮጲያን ለመፍጠር ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል ።
አረጋውያንም በበኩላቸው በልማት እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት እንዲሳተፉ እና የራሳቸውን የኑሮ ደረጃ እንዲያሻሽሉ ምቹ ሁኔታ ሊፈጠርላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል ። በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለሀገር ባለውለታ ለሆኑ አረጋውያን ተገቢውን ክብር፣ ፍቅር እና እንክብካቤ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል በመድረኩ እዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ ፣ፀሀፈ ተውኔት አያልነህ ሙላት እና ልጅ ዳንኤል ጆቴ የተለያዩ እውቀትና ልምድ ያላቸው አተሞክሮዋቸውንና የእውቀት ክህሎትና የህይወት ጉዞ በዕለቱ ለተገኙት ወጣቶችና ታዳሚዎች አስቃኝተዋል ።
