የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶች ተሳትፎ መብት ጥበቃና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶች ተሳትፎ መብት ጥበቃና ተጠቃሚነት ዙሪያ ከኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።

‎‎ስምምነቱን የኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ፈርመዋል። ተቋማቱ ከለውጡ ወዲህ ሰፋፊ ሪፎርም በማካሄድ የሴቶችን ትግል ከማቀጣጠል ጎን ለጎን በየዘርፉ ያላቸውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን በተናጠልና በጋራ ሲያከናውኑ መቆየታቸው በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል። የተጀመረውን ውጤታማ ስራ የበለጠ አጠናክሮ በማስቀጠል በዘርፉ የሚጨበጥ ወጤት ለማስመዝገብ በትብብር መስራት ወሳኝ መሆኑንና የመግባቢያ ስምምነቱም የዚሁ አካል መሆኑ ተጠቅሷል። የስምምነቱ ዋና ዓላማ በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብርና ቅንጅታዊ አሰራር የበለጠ በማጠናከር የሴቶችን ተሳትፎ፣ መብት ጥበቃና ተጠቃሚነት ለማጎልበት ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።

‎‎በቀጣይም ስምምነቱን መሠረት በማድረግ ተቋማዊ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት በትጋት እንደሚሰሩ የስራ ሃላፊዎቹ አረጋግጠዋል። ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በአፍሪካ ምርጥ አፈጻጸም ያሳዩ ሚኒስትር” ተብለው መሸለማቸው የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

Please follow and like us: