‎የማህበራዊ አገልግሎት እና ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ባለፉት የለውጥ ዓመታት ተጨባጭ ስኬቶች ማስመዝገብ ተችሏል

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ አኳያ ተጨባጭ ስኬቶች መመዝብ ችለዋል። ‎ከተገኙ ስኬቶች መካከልም በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ተጋላጭ ለሆኑ 10 ሚሊዮን 524 ሺህ 466 ዜጎች በከተማና የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም አማካኝነት በአይነት እንዲሁም ከ3.4 ቢሊዮን በላይ የቀጥታ ድጋፍ መደረጉ ይጠቀሳል። ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 145 ሺህ 510 ዜጎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ድጋፎችን በመስጠት ከቤተሰቦቻቸው እና ከማህበረሰቡ ጋር የማቀላቀል ስራ መስራት ተችሏል።
‎
‎615 ሺህ 038 አካል ጉዳተኛ ዜጎች የተሃድሶ አገልግሎት እንዲያገኙ ሲደረግ 770 ሺህ 675 ተጋላጭ አረጋውያን አስፈላጊው ድጋፍና ክብካቤ እንዲያገኙ፣ መስራት የሚችሉ ደግሞ ምርታማ ሆነው ራሳቸውን እንዲችሉ ተደርጓል። ‎28 ሺህ 723 እድሮችና መሠል አደረጃጀቶች ድሃና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ልዩ ድጋፎችን በማቅረብ ማህበራዊ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ የተዘረጋው አሰራር ውጤት አስገኝቷል።
‎
‎በተጨማሪም የማህበረሰብ እንክብካቤ ጥምረቶች በማሳመንና በማስተባበር 3 ቢሊዮን 269 ሚሊዮን 949 ሺህ 670 በዓይነትና በገንዘብ ሀብት በማሰባሰብ ድሃና ተጋላጭ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ መደረጉን ገልፀው፥ ይህም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅዖ አበርክቷል።
‎
‎በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተቀረፀው “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” የሚለውን ኢኒሼቲቭ መሠረት በማድረግ በተሰራው ጠንካራ ስራ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበረው 27 ሚሊዮን ተረጂ ቁጥር አሁን ላይ ወደ 3 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱ ትልቅ ሀገራዊ ስኬት ነው።
‎

Please follow and like us: