Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የህፃናት መብትና ደህንነት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤት እያስመዘገቡ ነው -ክብርት ሂክማ ከይረዲን
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከSOS Children’s Village ጋር በመሆን በህጻናት መብትና ጥበቃ ላይ የተዘጋጁ ሰነዶችን የማስተዋወቂያ እና ግብዓት የማሰባሰቢያ መርሀ-ግብር ተካሂዷል።
መርሀ-ግብሩ ላይ ከሁለቱ የከተማ አስተዳደር እና ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች እና አጋር ድርጅቶች ተሳትፈዋል። የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሂክማ ከይረዲን የህፃናት መብት፣ ደህንነት፣ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጸዋል። የህፃናትን ተግባራት ለማቀላጠፍና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችንና ማንዋሎችን በማዘጋጀት እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት በስራ ላይ እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል። የህፃናት ፖሊሲ እና የቅድመ ልጅነት ፖሊሲዎች በሀገራችን ያሉ ህፃናትን የትምህርትና የጤና ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል።
የማህበረሰብ ውይይት ማንዋሉን እና ሌሎች የአሰራር ማዕቀፎቹን እስከታች በማውረድ ለህፃናት መብትና ደህንነት መጠበቅ ሁሉ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የህጻናት ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የማህበረሰብ ውይይት ማንዋል ይፋ ተደርጓል። የህፃናት የተጠቃለለ ህግ ለማዘጋጀት የተደረገ የዳሰሳ ጥናት እንዲሁም የህጻናት መብትና ጥበቃ አዋጅ የመጨረሻ ረቂቅ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ማድረግ ተችሏል።
