Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሁሉንም ዜጎች ያካተተና የፆታ እና ማህበራዊ አካታችነት የጠበቀ ለማድረግ የትብብርና የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ አካል ጉዳተኛ ዜጎች የሚውል የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶችንና የህፃናት ጋሪዎችን ባስረከቡበት ወቅት እንደገለፁት ማዕከሉ የዜጎችን ክብር እኩልነትና ተደራሽነት አገልግሎት የማግኘት መብት ለማረጋገጥ በአካታችነት ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
አገልግሎቱን ይበልጥ የተሟላ ለማድረግ በጋራ ሊሰሩባቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፣ የብሔራዊ ማህበራዊ መዝገብ Social Registry) አሰራር ወደ መሶብ ማዕከል እንዲካተት በትኩረት በመሰራት ላይ እንደሆነ ገልፀዋል።ሚኒስቴር መ/ቤቱ የማዕከሉን አገልግሎት ይበልጥ ለማጠናከርና አገልግሎቱ ሁሉንም ዜጎች ያካተተና የፆታ እና ማህበራዊ አካታችነት ለማድረግ የትብብርና የቅንጅት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። በቀጣይም የአካል ጉዳተኞችን ለመደገፍ የሚያስችሉ የአካል ድጋፍ መሣሪያዎችን ለሁሉም የመሶብ አገልግሎት ቦታዎች ለማድረስና በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል።
የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው የመሶብ አንድ መስኮት ማዕከል አገልግሎቱን ፍጹም ተደራሽ፣ ፍትሃዊ እና ሁሉንም ዜጎች ያካተተ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል ። ማዕከሉ ለአካል ጉዳተኞች፣ ለሴቶች፣ ለአረጋውያን እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቅድሚያ የሚሰጥ አሰራር በመዘርጋት የዜጎችን እኩልነት እና ሰብአዊ ክብር ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። በመጨረሻም አንድ ማዕከል ማለት አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን፣ የእያንዳንዱን ዜጋ ክብር፣ እሴት እና አቅም መገንዘብ እና ልማት ለሁሉም እኩል እንዲደርስ ለማድረግ ሁለቱ አካላት የመግባቢያ ስምምነት በመፈረም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ።
