‎የስርዓተ ጾታ እኩልነትንና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተተገበረ ያለው የተቋማት የአካቶ ትግበራ አበረታች ውጤት አስመዝግቧል

የስርዓተ ፆታ እና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ የሰብዓዊ መብት፣ የማህበራዊ ፍትህ፣ የእኩልነት እና የልማት ጉዳይ ነው። ለዚህም መንግስት ባለፉት የለውጥ አመታት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሂደቱን ለማጠናከር ሰፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። ለአብነትም በሴክተር መ/ቤቶች አደረጃጀቱ እንዲዋቀር እና በሰው ኃይል እንዲደራጅ በማድረግና እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታትና ፍትሃዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲሰፍን ለማስቻል ሰፊ ጥረት ተደርጓል። ‎የተለያዩ የአሰራር ማዕቀፎች ተዘጋጅተው በስራ ላይ እንዲውሉ መደረጉ በሴቶች፣ ህፃናት፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያንና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ ዙሪያ የወጡ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች ወደ ታች ወርደውና ተቋማዊ ሆነው እንዲሰሩ ከማድረግ ባሻገር ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛል፡፡
‎
‎የእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ጉዳይ በሁሉም ዘርፍ ትኩረት ከመስጠት ባሻገር እስካሁን በተደረገው ጥረት 164 የመንግስት ተቋማት ጉዳያቸውን አካታች በሆነ መልኩ በመተግበር ረገድ አበረታች ውጤቶች ተመዝግበዋል። ‎እንደሀገር የአካቶ ትግበራው እንዲሳለጥ እና እነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሂደቱ የእኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል መዋቅሩን ከማጠናከር ጎን ለጎን  በቁርጠኝነት መስራት እና መምራት ከሁሉም አስፈጻሚ አካላት ይጠበቃል።
‎
‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደፊትም ለአካቶ ትግበራ ውጤታማነት አመቺ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት፣ የተቋማትን አቅም በመገንባት፣ ቅንጅትና ትብብርን በማጠናከር የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን በማድረግ እንዲሁም የአፈጻጸም ደረጃን በመለካት ተጠያቂነትን ለማስፈን በትኩረት የሚሰራ ይሆናል።
‎

Please follow and like us: