Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ እና የህጻናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) ጋር የ5 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ
የኢፌድሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የህጻናት ኢንቨስትመንት ፈንድ ፋውንዴሽን (CIFF) በኢትዮጵያ ያለውን የሴት ልጅ ግርዛትንና ያለዕድሜ ጋብቻን ለማስቆም የሚያስችል የ5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ፕሮጀክት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

ፕሮጀክቱ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በዋናነትም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ ባሉ በተለዩ የችግሩ ተጋላጭነት ያላቸው አካባቢዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ይተገበራል።
ሲአይኤፍኤፍ (CIFF) ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪ ማዕከላዊ የክትትልና ግምገማ ዲጂታል የመረጃ ቋት እና ዳሽቦርድ ለመዘርጋት የቴክኒክ እገዛ ያደርጋል።

የስምምነቱን አፈጻጸም ለመከታተል በሁለቱ ተቋማት የሚመራ የጋራ ንዑስ ኮሚቴ በማቋቋም ስራዎችን በቅርበት ይገመግማል። በክትትል ሂደቱም የህጻናት ጋብቻ መቀነስ፣ የተቋረጡ ጋብቻዎች ቁጥር፣ የሴት ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቅ ምጣኔ እና “ከግርዛት” የሆኑ ቀበሌዎች መፈጠር እንደ ዋና የአፈጻጸም መለኪያ (KPIs) ሆነው ያገለግላሉ።
Please follow and like us:
