Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የዜጎቻችንን ማህበራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ እና ሀገራዊ አቅማችንን አቀናጅቶ በመጠቀም የዜጎቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይም በማተኮር መሥራት ይገባል -ክብርት ሁሪያ አሊ
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ይህን የገለፁት “An Assessment of the PSNP-5 and CBHI Linkage in LASS Focused Woredas” በሚል ርዕስ የተጠናው ጥናት ሪፖርትና ዋና ዋና ግኝቶች ይፋ በተደረጉበት መድረክ ነው።
በሰው ተኮር ስራዎች በተለይ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶችን በራስ አቅም በመፍታት ፈተናዎችን መሻገር ይገባል ብለዋል።
የዜጎቻችን ማህበራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ እና ሀገራዊ አቅማችንን አቀናጅቶ በመጠቀም የዜጎቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የቅድመ መከላከል ስራዎች ላይም በማተኮር እንደሚሠራም ጠቅሰዋል። በገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት እጅግ አበረታች ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም አሁንም በተጠቃሚዎች ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅት የሚያጋጥሙዋቸውን ችግሮች ለመፍታትና በቀጣይ የተጠቃሚዎችን ህይወት በዘላቂነት መለወጥ በትግበራ ወቅት የተስተዋሉ የአሰራር ችግሮች፣ ክፍተቶችና መዘግየቶች መቅረፍ ይገባል ብለዋል።
መንግስት የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎትን ስራዎች መካከል የሴፍቲኔት የቀጥታ ድጋፍ የካሽ ትራንስፈር (Cash Transfer) መርሃ-ግብር ተጠቃሽ ነው። በፕሮግራሙ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ህይወት ላይ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት የካሽ ትራንስፈር ድጋፍ በተጨማሪ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ትስስርን አጠናክሮ ማስቀጠልም እንደሚገባ ገልፀዋል። ይህ እንዲሆን ደግሞ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ስትራቴጂካዊ አጋሮቻች ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር መሥራት ይገባል ብለዋል።
