‎”ከምርጫ ድል ማግስት፤ ጠንካራ መንግስት” በሚል መሪ ቃል በፌዴራል ተቋማት የማህበራዊ ክላስተር ከፍተኛ አመራሮች መድረክ ተካሂዷል።‎

መድረኩ በሀገር ደረጃ በከፍተኛ ስኬት የተጠናቀቀውን የ7ተኛዉ ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ምርጫና የምርጫ ስራዎች አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ የድህረ ምርጫ ግቦች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል።

‎የ7ተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሂደት ለማደናቀፍ የዉስጥና የዉጭ ፀረ-ሰላም ኃይሎች በተቀናጀ መንገድ ቢንቀሳቀሱም «ኢትዮጵያ መርጣለች» የሚል ጠንካራ መልዕክት የተላለፈበት ውጤታማ ምርጫ መካሄዱ ተገልጿል። ‎ምርጫው ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መልኩ ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ተአማኒና የኢትዮጵያ አሸናፊነት የተረጋገጠበት ሆኖ መጠናቀቁም ተጠቅሷል።

‎‎የማህበራዊ ክላስተር ፖለቲካ ዘርፍ ሰብሳቢ ሽዊት ሻንካ ብልፅግና በምርጫው ሂደት የተለያዩ ግቦችን ይዞ በመንቀሳቀስ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ነፃ ምርጫ ማካሄድ እንደተቻለ ገልፀዋል።

‎የምርጫው ስኬት ጊዜ ተወስዶበት በተሰራ የቅድመ ምርጫ ስራና ብቃት ያለው የአመራር ስርዓት በመዘርጋት የተገኘ፣ ከማኒፌስት ትዉዉቅ ጀምሮ የቃል ኪዳን ሰነድ የታደሰበት ሂደት መሆኑን አስገንዝበዋል። ‎‎በፓርቲው የፊት መሪነት፣ በደጋፊው ቁርጠኝነት፣ በአባሉ ተጋድሎና በሕዝቡ ይሁንታ የተገኘ የመደመር ዉጤት ማሳያ ድል መሆኑን የማህበራዊ አድርጃጀት ዝርፍ ስብሳቢ ዶክተር ኤርጎጌ ጠቁመዋል። ‎መድረኩ በምርጫው ሂደት የታዩ ጥንካሬዎችን እና ጉድለቶችን በጥልቀት በመፈተሽ አመራሩ ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁ የሚሆንበት ነዉ መባሉን የገለፀው ብልፅግና ፓርቲ ነው።

Please follow and like us: