‎የሀብት ምንጫችንን በማስፋት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን በዘላቂነት መደገፍ የሚያስችል ሀገር በቀል አቅም እየተገነባ መሆኑን የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ገለፁ

በኦሮሚያ ክልል በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጀክት ትግበራ ውጤታማ የሆኑ የቋሚና ቀጥታ ድጋፍ ማህበራዊ አገልግሎቶች ትስስር የቀረቡበትና የተጠቃሚዎች የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል የተደረገበት ሂደት ምልከታ ተደርጎበታል።

‎‎የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ መንግስት የዜጎችን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭነት በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችል ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም በመቅረፅ ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል። ‎በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ274 ሺህ በላይ የቋሚ ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ ዜጎችን በማቀፍ ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። ‎ሆኖም የማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎቶች ይበልጥ ውጤታማ የሚሆኑት በተደራጀ የአሰራር ሥርዓት ሲመሩ እና ከሀገር ውስጥ በሚገኝ የሃብት ምንጭ በዘላቂነት መደገፍ ሲችሉ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎‎የሀብት ምንጫችንን በማስፋት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን በዘላቂነት መደገፍ የሚያስችል ሀገር በቀል አቅም እየተገነባ መሆኑን ገልፀዋል። በተጨማሪም ዜጎችን ከእርዳታ ጥገኝነት አውጥተው በራስ አቅም እንዲቆሙ ያስቻሉ መልካም ተሞክሮዎችን በአግባቡ መቅሰምና ማስፋፋት ይኖርብናል ብለዋል። የመርሐግብሩ ተሳታፊዎች በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የተገኘውን ስኬታማ ልምድ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም በትጋትና በውጤታማነት ሊተገብሩ እንደሚገባ በአፅዕኖት አሳስበዋል።
‎

Please follow and like us: