አለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት መጀመሩ ተገለፀ::

በመጪው ዓመት ህዳር 2019 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸው ተገለፀ::

በመጪው ዓመት ህዳር 2019 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጀመራቸው ተመላክቷል :: የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር: የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ: የፌዴሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎች እና የክልሉ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ስለቅድመ ዝግጅት ስራዎች ምክክር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይነህ ጉጆ በምክክሩ ላይ እንዳሳሰቡት፣ በዓሉ በርካታ እንግዶች ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚሳተፉበት በመሆኑ፣ ወገኖቻችን በጉዞም ሆነ በማረፊያ ቦታዎች ላይ ምንም ዓይነት መጉላላት እንዳይደርስባቸውና የትራንስፖርት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ እንዲሁም የሆቴል መሠረተ ልማቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆናቸውን ከወዲሁ ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል::

የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ዝግጅቱን ከዚህ ቀደም ከነበሩት በዓላት በላቀ መልኩ የደመቀ ለማድረግ ስራዎች መጀመራችውን መግለፃቸውን ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Please follow and like us: