‎”የኢትዮጵያ መንግስት ለማህበራዊ ጥበቃ ስራዎች ትኩረት በመስጠት ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት የሚሆኑ ናቸው” – አምባሳደር አማ ቱወመ – አሞሃ

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የአፍሪካ ህብረት የጤና፣ ሰብዓዊ ጉዳዮችና የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር አማ ቱወመ- አሞሃ ሊካሄድ በታቀደው የአፍሪካ ማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በሰፊው ተወያይተዋል።

‎‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ወቅት፥ አፍሪካ የእምቅ ሀብት ባለቤት መሆኗን በመጥቀስ ያላትን ሀብት፣ ሀገር በቀል እውቀትና በጎ እሴቶቿን ለአህጉሪቱ ችግሮች መፍቻነት ማዋልና የምንመኛትን አህጉር እውን ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።‎ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት በመዘርጋት የዜጎችን ህይወት ለማሻሻል ትላልቅ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በርካታ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን በሰፊው አብራርተዋል፤ የአፍሪካ ሕብረት እያደረገ ላለው ጠንካራ ትብብርና አጋርነት ከፍ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። ‎በቀጣይም በአህጉር ደረጃ ሀገራት ልምዳቸውን የሚለዋወጡበት፣ ጠንካራ ትስስርንና ትብብርን የሚፈጥሩበት እንዲሁም ፖሊሲ አውጪዎችና የሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት የሚሳተፉበት የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ በጋራ ለማዘጋጀት መታቀዱን ገልፀው፥ ህብረቱ ለዝግጅቱ ጠንካራ የቴክኒክ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

‎‎የአፍሪካ ህብረት የጤና፣ ሰብዓዊ ጉዳዮችና የማህበራዊ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር አማ ቱመ- አሞሃ በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ መንግስት ለማህበራዊ ጥበቃ ስራዎች ትከረት በመስጠት እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተምሳሌት የሚሆኑ ናቸው ሲሉ አድናቆታቸውን ገልፀዋል። ‎በአህጉር ደረጃ የማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ በጋራ ለማካሄድ በሚኒስቴሩ የቀረበውን ጥያቄ የተቀበሉ መሆኑን እና በመድረኩ የኢትዮጵያን ተሞክሮ ለሌሎች ሀገራት ለማካፈል ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

Please follow and like us: