‎የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ሪጅናል ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ኒሃን ኤርዶጋን በስደተኞች ምላሽ መስጫ ማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያስችል አጋርነትን የበለጠ ለማጠናከርና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑ ገለፁ

በሱማሌ ክልል ቶጎ ውጫሌ የሚገኘው የፍልሰተኞች ምላሽ መስጫ ማዕከል የስራ ጉብኝት ተካሄደ።

‎‎በጉብኝቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊን ጨሞሮ የአይ ኦ ኤም (IOM) ሪጅናል ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ኒሃን ኤርዶጋን፣ በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቢባቱ ዋኔ-ፎል፣ እንዲሁሞ ሌሎች የአይ ኦ ኤም እና የሱማሌ ክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። ‎ልዑካኑ በክልሉ ለፍልሰተኞች ከሚሰጡ አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት፣ የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ተግዳሮቶችና መፍትሔዎቹ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የአለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ባለሙያዎች ጋር በሰፊው ተወያይተዋል። ‎በጉብኝቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ፣ በማዕከሉ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ የተቀናጀ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን መመልከት መቻሉን ገልፀዋል።

‎መንግስት ደህንነቱ የተጠበቀ መደበኛ ፍልሰትን ለማበረታታትና መደበኛ ካልሆነ ፍልሰት ጋር የተያያዙ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ የጀመራቸውን ስራዎች ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (ከአይ ኦ ኤም) እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። ‎የአይ ኦ ኤም (IOM) ሪጅናል ምክትል ዳይሬክተር ሚስ ኒሃን በበኩላቸው፥ በጉብኝቱ በተመለከቱት ተግባር መደሰታቸውን ገልፀው፤ ወደፊትም ከስደት ተመላሽ ዜጎች ወደ ቀደመ ኑሮኣቸው እንዲመለሱና ህይወታቸውን በዘላቂነት እንዲለወጥ እንዲሁም በምላሽ መስጫ ማዕከላት የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው አይ ኦ ኤም አጋርነት የበለጠ ለማጠናከርና በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
‎

Please follow and like us: