በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 672 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

‎‎በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 670 ወንዶች እና1 ሴት እንዲሁም 1 ጨቅላ ህፃን ሲሆን ከተመላሾች መካከል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ 34 ታዳጊዎች ይገኙበታል። መስከረም 5/ 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ90 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
‎
‎ሚኒስቴሩ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ ፍልሰትን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ወደ ተለያዩ ሀገራት ሄደው የሚመለሱ የፍልሰት ተጎጂዎችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋምም በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
‎
‎በተለያዩ ጊዜያትም ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
‎

Please follow and like us: