Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የልጆችን አዕምሮአዊ፣ አካላዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት በሳይንሳዊ መንገድ በማገዝ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል - ክብርት ሒክማ ከይረዲን
የህፃናት ተንከባካቢዎች የሙያ ደረጃ፣ ስርዓተ ስልጠናና የማሰልጠኛ ማኑዋል ይፋዊ የማስጀመሪያ መርሐግብር ተካሂዷል።
በመርሐግብሩ ላይ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሒክማ ከይረዲን እንዳሉት፥ ህፃናት የነገ ሀገር ብሩህ ተስፋ ናቸው። ህፃናት ላይ የምናደርጋቸው ኢንቨስትመንቶች ቀጣይነት ላለው ሀገራዊ ዕድገት እና ኢኮኖሚ ድርሻው የጎላና ሃላፊነትንም መወጣት መሆኑንም ገልጸዋል። የታዳጊ ሕጻናት እድገት የሚወሰነው በተለይ በቀዳማይ የልጅነት ጊዜ ምዕራፍ በመሆኑ መንግስት የልጆችን አዕምሮአዊ፣ አካላዊ እና ማኅበራዊ ዕድገት በሳይንሳዊ መንገድ በማገዝ ብቁ ትውልድ ለመገንባት በትኩረት እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል። የቀዳማይ ልጅነት እድገትና ክብካቤ ፓሊሲና ማስፈፀሚያ ማዕቀፎች ተቀርፀው ከ2015 ወዲህ በቅንጅት እየተተገበሩ በመሆናቸው በህፃናት አመለካከት፣ አያያዝና እንክብካቤ ዙሪያ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

ይሁንና ህፃናትን በመንከባከብ ረገድ በሀገራችን ደረጃውን የጠበቀና በዘላቂነት አገልግሎት የሚሰጡ የበቁ ሙያተኛ ክፍተት መኖሩን ጠቅሰዋል። የስልጠናና የማሰልጠኛ ማኑዋል ሰነዱ ብቁና ተወዳዳሪ ሙያተኛ ለማፍራት ብሎም ጥራትና ወጥነት ያለው የህፃናት እንክብካቤ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል። ለሰነድ ዝግጅቱም ሆኖ እንደሀገር ለህፃናት መብትና ደህንነት መጠበቅ ጉልህ አስተዋፅዖ እያበረከቱ ያሉ ባለድርሻና አጋር አካላትን አመስግነዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ክቡር አቶ አዝመራው ከበደ በበኩላቸው፥ የልጆችን ጥበቃ፣ እንክብካቤና ዕድገት የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ባሻገር መምህራንን ለማዘጋጀትና ተቋማትን አቅም ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ብለዋል። በመርሐ ግብሩ የሰነድ ዝግጅት ሂደትና ይዘት ላይ ያተኮረ ገለፃ የተደረገና ጉልህ ድርሻ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት እውቅና የሰጠ ሲሆን፤ በመድረኩ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከፓርተነርሺፕ ፎር ቼንጅ እንዲሁም ከሁሉም የክልል የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።Please follow and like us: