Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ኢትዮጵያና ማላዊ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከል የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያና ማላዊ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትንና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ መከላከልና የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ ፈርመዋል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በዚሁ ወቅት፥ ፍልሰትን በአግባቡ ማስተዳደር ከተቻለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠንና እና ቀጠናዊ ውህደትን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልፀዋል። በአንፃሩ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት በዜጎችንና በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብለዋል። ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራውን ብሔራዊ ምክር ቤትን ጨምሮ በጠንካራ የፖሊሲ፣ የሕግ እና ተቋማዊ አደረጃጀቶች አማካኝነት መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከል ያላሰለሰ ጥረት እያደረገች ትገኛለች ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለፍልሰት ምንጭ፣ መጓጓዣ እና መዳረሻ ሀገር እንዲሁም ማላዊ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚወስደው ደቡባዊ መንገድ ዋና ኮሪደርና ወሳኝ የመጓጓዣ መስመር መሆኗን አንስተዋል። ማላዊ የፍልሰት ተጓጂዎችን በማስጠለል፣ ወደ ሀገር እንዲመለሱ በማድረግ እንዲሁም የተደራጁ ወንጀለኞችን ለፍትህ በማቅረብ ሂደት እያበረከተች ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል። ስምምነቱ ሀገራቱ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትንና በሰዎች የመነገድ ወንጀል የተሰማሩ አካላትን ለመዋጋት፣ ጤናማ የፍልሰት አስተዳደርን ለማስፈን፣ ዜጎቻችንን ለመጠበቅና ተጎጂዎችን ለመደገፍ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክረን ለማስቀጠልና የጋራ ግዴታችንን ለመወጣት ያግዛል ብለዋል።

የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብርና አጋርነት የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን ገልፀው፥ ዜጎችን ለመታደግና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን ለማስቆም ማላዊ በቁርጠኛነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።
የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብርና አጋርነት የበለጠ እየተጠናከረ መምጣቱን ማሳያ መሆኑን ገልፀው፥ ዜጎችን ለመታደግና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀልን ለማስቆም ማላዊ በቁርጠኛነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል።Please follow and like us: