‎የቅድመ ልጅነት እድገት አስተግባሪ አካላት ፖሊሲ ማዕቀፍ እና የቅድመ ልጅነት እንክብካቤ ማስተግበሪያ ሰነዶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ

‎ከኦሮሚያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም ከጤና፣ ከትምህርትና ከተማ ልማት ቢሮዎች ከክልል፣ ከዞንና ከወረዳ ለተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በቅድመ ልጅነት እድገት ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
‎በፕሮግራሙ መክፈቻ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህፃናት መብትና ጥበቃ መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሮ ዘቢደር ቦጋለ እንደገለፁት፥ የቅድመ ልጅነት ከፅንስ እስከ 6 ዓመት እድሜ ክልል ላይ ላሉ ህፃናት በትኩረት በመስራት ብቁ እና ተተኪ ትውልድ ለማፍራት የሚያስችል ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑን ተናግረዋል። በዘርፉ ኢንቨስት የሚደረግ የሰው ሀይልና ሀብት በምላሹ በብዙ እጥፍ ትርፋማ የሚያደርግ፣ ለሀገር ግንባታ እንዲሁም የድህነትን ሰንሰለትን ለመበጠስ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህም የቅድመ ልጅነት ዘመንና ትምህርት ፖሊሲ በጤና፣ በትምህርትና ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀና በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ከህፃናት መብት፣ ደህንነትና ተጠቃሚነት አኳያ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡ ‎በመሆኑም ፖሊሲውን በመቀናጀት፣ በመደጋገፍና በመናበብ በእውቀት መምራት እንዲያስችል ለአስፈፃሚ አካላት በቂ ግንዘቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
‎በመድረኩ ላይ በዋናነት የቅድመ ልጅነት እድገት ምንነት፣ ጠቀሜታ እንዲሁም በቤተሰብ፣ በህፃናት እንክብካቤ ማዕከላት፣ በትምህርት ቤቶች ላይ ስላለው አተገባበር ገለፃ ተደርጓል። በተጨማሪም የህፃናት የቀን ማቆያ ስታንዳርድ፣ አዎንታዊ የህፃናት አያያዝና አስተዳደግ፣ እና የባለድርሻ አካላት ሚና አስመልክቶ የተዘጋጁ ሰነዶችን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል። ‎በቀጣይ በክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ስልጠናውን እሰከታችኛው መዋቅር ማወረድና በሁሉም አስተግባሪ ሴክተሮች ተግባራዊ እንዲደረግ አቅጣጫ በመስጠት ወደተግባር እንደሚገቡ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
‎
‎የኦሮሚያ ክልል የሴቶችና ህፃናት ቢሮ የህፃናት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሰርካለም ሳኩሜ በበኩላቸው፥ የህፃናት የቅድመ ልጅነት ፕሮግራም ተግባራት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር የሚጠይቅ በመሆኑን የጋራ ርብርቡ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
Please follow and like us: