የቤተሰብ _ጉባኤ ምንነት፣ ጠቀሜታና መንገዶቹ (ክፍል ሁለት)

የቤተሰብ ጉባኤ (Family Council) የቤተሰብ አባላት በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ በሚያደርጉት የጋራ የግንኙነት ጊዜ የሚካሔድ የቤተሰብ አባላት የውይይት መርሃ ግብር ነው። በዚህ ጉባኤ የቤተሰቡ ጉዳዮች በሙሉ ተነስተው ውይይት ይደረግባቸዋል።
‎
‎የቤተሰቡ አባላት ሃሳብ በመስጠት ተሳትፎ የሚያደርጉ ሲሆን ማንኛውም የቤተሰብ ጉዳይ በአንድ ድምጽ እንዲረጋ የሚያስችል ስምምነት ይደረስበታል።
‎
‎
‎በቤተሰብ ጉባኤ የቤተሰብ አባላት ስኬት እና ያሉበት ደረጃ፤ በአባላቱ ላይ የሚደርስ ችግር እና መፍትሔው፤ በቤት ውስጥ ስለሚኖር የቀጣይ ጊዜ የጋራ ጉዳይ እና የሥራ ክፍፍል ላይ ሁሉም አባላት ተሳትፈው ውይይት ይደረጋል። በውይይቱ ውጤትም የቤተሰብ የጋራ ጉዳዮች፣ ፈታኝ ሁኔታዎች እና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተለይተው ይታወቃሉ።
‎
‎ለቤተሰብ ግንኙነት እና ትስስር የቤተሰብ ጉባኤ ከፍ ያለ አስተዋጽኦ አለው። በሂደትም ጤናማ ቤተሰብ ለመፍጠር በእጅጉ ያግዛል።
‎
‎#በተጨማሪም_ከቤተሰብ አባላት ጋር ጊዜ ሠጥቶ በጋራ ማሳለፍ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል።
‎
‎• የቤተሰቡን አካላዊና አእምሮአዊ ጤንነት ይጠብቃል፣
‎• የልጆች የትምህርት አቀባበል ውጤታማ እንዲሆን ይረዳል፣
‎• በቤተሰብ ውስጥ የሚከሰትን የባህሪ ችግር ይቀርፋል፣
‎• በራስ የመተማመን ስሜትን ያሳድጋል፣
‎• ችግር የመፍታትን ክህሎት ያዳብራል፣
‎• ልጆች የወደፊት የመልካም ቤተሰብ ክህሎትን አርዓያነት እንዲከተሉ ያደርጋል፣
‎• የቤተሰቡን ፍቅር፣ መተሳሰብና መቀራረብ ያዳብራል፣
‎• አስቸጋሪ እና ፈታኝ ጊዜዎችን ለመቋቋም ይረዳል።
‎
‎
‎• የቤተሰብ ቀንን በቤት ውስጥ በማክበር፣
‎• የቤተሰብ የቤት ውስጥ ሥራዎችን ተከፋሎ በመስራት፣
‎• በበጎ ፈቃድ ተግባራት ላይ በመሳተፍ፣
‎• የእለት ውሎ ላይ መረጃ መለዋወጥ፣
‎• በጋራ መመገብ፣የጋራ የሻይ ቡና ጊዜ በማካሄድ፣
‎• የቤተሰብ አባላት ጤና፣ ባህሪ፣ ስነ-ልቦናና የትምህርት ሁኔታዎችን በመከታተል፣
‎• ለልጆች መጽሐፍትን ማንበብ፣
‎• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በጋራ በማድረግ፣
‎• ለመልካም ተግባራት እውቅና በመስጠትና በማበረታታት፣
‎• ልዩ ልዩ ቦታዎችን እና ዘመዶችን በመጎብኘት፣
‎• ማኅበራዊ ኩነቶች ላይ በጋራ በመሳተፍ፣
‎• የልጆችን ትምህርት ቤት መጎብኘት፣
Please follow and like us: