የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ብሔራዊ ማኅበራት በጋራ መሥራታቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋገጡ

የሴቶችን ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ጋር ባካሄደው የዕቅድ ማዋሀድ እና ውይይት፣ የአካል ጉዳተኞችን መብትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ላይ በመወያየት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባባት ፈጥረዋል፡፡
የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ድኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ከብሔራዊ የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ እንደገለጹት የጤና መድህንና ማህበራዊ ጥበቃ፦ በድህነት ውስጥ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን (CBHI) ሙሉ የህክምና ወጪ ሽፋን እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የቀረጥ ነፃ አገልግሎትን በተመለከተ አሰራሩን ይበልጥ በማዘመንና በማቀላጠፍ ወደ “መሶብ” (Masob) ዲጂታል ኢ-ሰርቪስ ተሸጋግሯል።
እንዲሁም የመረጃ ክፍተቶችን ለመቅረፍ “ብሔራዊ የማህበራዊ መዝገብ” (National Social Registry) እየተዘረጋ እንደሚገኝ ተቁመው የአካል ድጋፍ መሳሪያዎችን ተደራሽ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ድጋፍ ሰጪ መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ የማምረት ስራ ትኩረት በመስጠት ወደ ምርት መገባቱን ገልፀዋል።ፖሊሲና የሕግ ማእቀፎችን በተመለከተ አገራዊ የተጠቃለለ የአካል ጉዳተኞች ፖሊሲና የ10 ዓመት ድርጊት መርሃ ግብር እንዲፀድቁ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆነ ጠቁመዋል።
Please follow and like us: