Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የቀድሞዋ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ክብርት ወ/ሮ ሒክማ ከይሬዲን አዲስ ከተሾሙት የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክብርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ ጋር የስራ ርክክብ አደረጉ *በዘርፉ ለተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እናመሠግናለን!
የቀድሞዋ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ክብርት ወ/ሮ ሒክማ ከይሬዲን እና አዲስ የተሾሙት የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ በዛሬው ዕለት የስራ ርክክብ አደረገዋል።

በዚሁ ወቅትም ከዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ የተደረገ ሲሆን፥ በዘርፉ የሚገኙ የስራ ክፍሎች ያሉበትን ደረጃና አጠቃላይ ያከናወኗቸው ተግባራትን አስመልክቶ ሙያዊ ማብራርያ ቀርቧል። በተመሳሳይ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ያሏቸው ጉዳዮች ተነስተው ተወያይተዋል የሴቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ክቡርት ወ/ሮ ሄለን ደበበ በዘርፉ የሚከናወኑ ተግባራት በተናበበ መልኩ ሊመሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ የዘርፉን አፈፃፀም በማላቅ የተጣለበትን ተቋማዊና ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንዲችል ሁላችንም የራሳችንን አሻራ ማሳረፍ አለብን ብለዋል።

የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች በበኩላቸው፣ ክብርት ሚኒስትር ዴዔታ ሒክማ ከይሬዲን በአመራርነት ቆይታቸው በዘርፉ ለተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችና ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። የተሰጡትን አቅጣጫዎች መነሻ በማድረግና የቅንጅት አሰራርን በማጠናከር የታቀዱትን ግቦች ለማሳካት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አያይዘው ገልጸዋል።
Please follow and like us:
