በእውቀት ላይ የተመሠረተ የዲጂታል ክህሎት — ለነቃ ትውልድና ለጸናች ኢትዮጵያ!

ዓለም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ፈጣን ምጥቀት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ዕውቀትና የዲጂታል ክህሎት የሀገር ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን መሠረታዊ መሪዎች ናቸው!
‎
‎ኢትዮጵያን ወደተሻለ የዕድገት ከፍታ ለማሸጋገር፣ በዘመኑ የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የበቃ፣ መፍትሔ አመንጪና ንቁ ትውልድ መገንባት የቀደመ ተግባራችን ሊሆን ይገባል።
‎
‎💡 ለነቃ ትውልድ፦
‎👉የዲጂታል መሣሪያዎችንና ዕውቀቶችን በመጠቀም የፈጠራ አቅምን ማሳደግ፣
‎👉በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ኃይል መፍጠር ወሳኝ ነው።
‎
‎🏛️ ለጸናች ኢትዮጵያ፦
‎👉በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሀገርን የኢኮኖሚ አቅም ማጠናከር
‎👉በዳጂታል የታገዘ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የሆኑ አገልግቶችን ለሕዝባችን ማቅረብ
‎👉የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ጠንካራና በፈተናዎች የማይበገር ሀገራዊ መሠረት መጣል
‎
‎የእውቀትና የዲጂታል ክህሎት ጉዞ የሁላችንም አሻራ ይፈልጋል! ዛሬ የምንገነባው የዲጂታል አቅም የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ ያረጋግጣልና።
‎
‎🔗 በዕውቀት እንመራ! በዲጂታል ክህሎት እንበልፅግ! ሀገራችንን እናፅና!

Please follow and like us: