Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ የስራ ርክክብ እና የአመራር ቅብብሎሽ ሂደት
የሚኒስቴሩ የማህበራዊ ዘርፍ የስራ ርክክብ እና የአመራር ቅብብሎሽ ሂደት። የቀድሞ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ አዲስ ለተሾሙት ክብርት ኬሪያ ኢብራሂም የስራ ርክክብ አድርገዋል።

በርክክቡ ወቅት የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታዋ ክብርት ኬሪያ ኢብራሂም እንደገለፁት ስራዎችን አደራጅቶና ሰንዶ ለቀጣይ ባለአደራ ማስተላለፍ እምብዛም የማይስተዋል የነበረ መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ እንዲህ አይነቱ የፓለቲካ ልምምድ መቀጠል ያለበት ነወ። የቀረበላቸው ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ዘርፉ ጥልቅ መሆኑን የተሻለ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ገልፀው፥ በተሰጠን ጥቂት ጊዜና ሰፊ ዕድል የራሳችንን አበርክቶ ለሀገር በማስቀመጥ በዘርፉ የተጀመሩ ጥረቶችን ለማስቀጠልና አዲስ ውጤቶችን ለማስመዝገብ በከፍተኛ ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። የቀድሞዋ የዘርፉ ሚኒስቴር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ በበኩላቸው ስራዎችን በቅብብሎሽ መስራትን ልምድና ባህል በማድረግ ሀገርን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለአዲሷ ተሿሚ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተዋል።

በማህበራዊ ዘርፍ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት እንደ ሀገር ሰፊ ስራዎች የተከናወኑ መሆኑን አስታውሰው አሁንም ከአዲሱ አመራር ከፍተኛ ስራዎች እንደሚጠበቁ ገልፀዋል። ለነበሩት መልካም ጥረቶችና ስራዎች የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ አጋር ድርጅቶች፣ የክልል ሴክተር ቢሮዎች ፣ማህበራትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ላደረጉት ሙያዊ አበርክቶ አመስግነው በዘርፉ የሚከናወኑ አካታች ማህበራዊ አገልግሎቶችን አሁንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
