Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ከፅንስ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እስከ ማፍራት – ለሕፃናት ሁለገብ እድገት የተቀናጀና የተደመረ ጥረት”
በመደመር እሳቤ በተቃኘው አዲሱ የሴክተራችን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መሠረት በህፃናት ዘርፍ ልናሳካቸው የሚገቡ ውጤቶች በዋነኝነት አራት ናቸው። እነዚህም፦
👉 ብቁ፣ ጤናማና ፈጣሪ ትውልድ መፍጠር
👉 የወዲፊቱን የሀገር አቅም የሚሸከምና አልቆ የሚያስቀጥል ትውልድ መገንባት
👉 እያንዱንዱ ህፃን በምቾት ሁኔታ ውስጥ የማደግና የመለወጥ እኩል እድል እንዲያገኝ ማድረግ
👉እውቀት፣ እሴትንና ማንነትን የሚጠበቅ ሀገር ወዳድ ትውልድ መገንባት ናቸው።
እነዚህ እውን እንዲሆኑ ቤተሰብ፣ ማህበረሰብና ተቋማት ተገቢውን ትኩረት ሰጥተን፣ ተቀናጅተንና አቅማችን ደምረን በትጋ መስራትና የተጀመሩትንም የበለጠ አጠናክረን ማስቀጠል ይጠበቅብናል።
ሀገር የሚገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ እንደመሆኑ መጠን፥ ህፃናት ከፅንስ ጀምሮ ተገቢውን ክብካቤ እያገኙ የተሟላ ስብዕና ኖሯቸው፣ በመልካም ስነምግባርና በእውቀት ታንፀው እንዲያድጉና ሀገር እንዲረከቡ ማስቻል የሁላችንም ሃላፊነት ነው።
የህፃናት ጉዳይ ለነገ የምንተወውና በይደር የምናቆየው ሳይሆን በጊዜ የለንም መንፈስ በጣም መፍጠን፣ መፍጠርና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ካሰብነው ለመድረስ መዝለል ይኖርብናል።

ክብርት ወይዘሮ ጥሩማር አባተ
የህጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
Please follow and like us:
