የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረጃ ደህንነት አስተዳደር ጋር መግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢንፎርሜሽን መረጃ ደህንነት አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት መግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱ ዋና አላማ በኢንፎርሚሽን ቴክኖሎጂ እስትራቴጂ፤በቴክኖሎጂ መሰረተ ልማትና የአቅም ግንባታ ዘርፍ የተጠናከረ ስራ ለመስረት የታለመ ነው፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በፊርማ ስነስረዓቱ እንደገለፁት ዘመኑ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ትጥቅ መታጠቅና የሚኒስቴር መ/ቤቱን ሰፊ ስራ ለማሳለጥ ከኢንፎርሜሽን መረጃ ደህንነት አስተዳደር ጋር መስራት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረጃ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው አገራዊ ግቦችንና የህዝብን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ ለመስራትና የቴክኖሎጂ ባለቤት እንዲሁም የዲጂታል ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ ከተቋማት ጋር መስራት አስፈላጊ ሲሆን

በተለይም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እጅግ ሰፊ የሆነውን የህብረተሰብ ክፍል የሚያገለግል በመሆኑ ከዚህ መሰል ተቋም ጋር መስራት ደግሞ ለአገር የሚኖረው ጠቀሚታ እጅግ የላቀ ነው ብለዋል፡፡

 

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *