Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የ9 ወር የሥራ አፈፃፀም ውይይት ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር አድርጓል።
(ግንቦት 17 ቀን 2015 ዓ.ም)
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀሙን ከፍተኛ አመራሩና አጠቃላይ ሠራተኛው ገምግሟል።
ሚኒስቴር መሥርያ ቤቱ በ2015 ዓ.ም የጀት ዓመት 9 ወራት ድጋፍ በርካታ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑ ተገልጿል።
በማህበራዊ ድጋፍ ፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ በሴቶችና ህፃናት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ24 ሚሊዮን በላይ ወጣቶችን በተለያዮ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ከ 17 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አገልግሎት መስጠት ተችሏል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ማቋቋም መቻሉ ተችሏል።
ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ለመከላከል 61 ሺህ 324 ዜጎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ድጋፍ እንዲያገኙ መደረጉ ተገልጿል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡሙት በቀጣይ ማህበራዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ድጋፎችን ተደራሽ ማድረግ የሴቶችና ህፃናት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
Please follow and like us:
