በየዘርፉ የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ለውጡን ለማፅናት ሁሉም በተሰማራበት መስክ መረባረብ ይጠበቅበታል

የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው የ100 ቀናት አፈጻጸም የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በመድረኩ፤ በ2017 የመጀመሪያው 100 ቀናት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረጉን ተገልጿል። እንደሀገር መንግስት የወሰዳቸው የሪፎርም እና ዋና ዋና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ያላቸው ፋይዳ፣ የተገኙ ውጤቶችና አዝማማያዎቹ ምንድናቸውን የሚሉት በንፅፅር ተብራርቷል።

ባላፉት 3 ወራት በተሪዝም፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎትና በግብርና ዘርፍ የተቀመጠው እድገት የዚህ አመላካች መሆኑም ተመላክቷል። ሆኖም አለም አቀፍና አህጉራዊ ብሎም ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ተፅዕኖች በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ፈተና መደቀኑ ተጠቁሟል።

መንግስት የተጀመሩትን የለውጥ ስራዎች ወደ ተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም በማሸጋገርና የበለጠ አጠንክሮ በማስቀጠል የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታትና ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። እንደሀገር የተመዘገበው ውጤቱ የሁላችንም ድምር ውጤት መሆኑን መጥቀስ በቀጣይም የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ለውጡን ለማፅናት ሁሉም በተሰማራበት መስክ መረባረብ እንዳለበት የስራ ኃላፊዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እንደ ዜጋ የእኔ ሚና ምንድን ነው የሚለውን ከመገንዘብ ባሻገር የራሳችንን ትጋት መጨመር፣ የመንግስትን ጥረቶች መደገፍና ለለውጡ ተባባሪ መሆን ያስፈልጋል ተብሏል።

 

Please follow and like us: