ሚኒስቴሩ መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በመጎብኘት የ8ሺህ ኪሎ የሚመዝን የቴምር ድጋፍ አደረገ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመጎብኘት የ8ሺህ ኪሎ ቴምር ድጋፍ አድርጓል።

በዕለቱ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስተር የተመራው ልዑክ እንደገለፀው ፤ ተቋሙ ከዚህም በላይ ዜጎችን ተደራሽ እንዲያደርግ ቋሚ ኮሚቴውና ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የድጋፍና ክትትል ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው እየሠራ ያለውም ስራ የመንግስትን ሸክም ያቀለለና የሚመሰገን ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል። ከጎዳና ተነስተው በማዕከሉ እንክብካቤ ወደ ተሻለ የኑሮ ደረጃ የደረሱት የእእምሮ ህሙማንና አረጋውያን የመቄዶንያ ቤተሰቦች ፣ እንደሀገር ይበልጥ ትኩረት ሰጥተን ብንሠራ ዜጎች መለወጥና መስራት እንደሚችሉ ማሣያ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተቋሙን ለማጠናከር በጋራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።እንደሜቄዶንያ አይነት ተቋማትን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግና ልምድም እንዲቀስሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ማዕከሉ ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ በርካታ ዜጎች ከጎዳና ላይ ተነስተው አዲስ አበባን ጨምሮ በየክልሉ ባሉት የማቋቋሚያ ማዕከላት መሰረታዊ የምግብ፣ መጠለያ ፣አልባሳትና የህክምና አገልግሎት እየተሰጣቸው መሆኑን ጠቅሶ ከዚህ በተጨማሪ ለአረጋውያን እና ለአእምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ልዮ ትኩረት በመስጠት እየሠራ መሆኑ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል። መቄዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ስራውን በ40 ሰዎች በመጀመር በአሁኑ ሰዓት ከ8500 በላይ ሰዎችን በአዲስ አበባ እና በክልል ቅርንጫፎች በመርዳት ላይ የሚገኝ ሲሆን 2 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ሆስፒታል እና የአረጋዊያን ማረፊያም እየገነባ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ወቅት ማየት ተችሏል።

 

Please follow and like us: