ነገ በሚጀመረው የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እንግዶች አዲስ አበባ ገቡ

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የወጣት ሚኒስትሮችና ወጣት አመራሮች በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚካሄደው የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

እንግዶች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሴቶችና እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሙና አህመድ እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት ፉአድ ገና አቀባበል አድርገውላቸዋል። የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ “የወጣቶችን አቅም – ለበለፀገች አፍሪካ” በሚል መሪ ሃሳብ ከመጋቢት 25 እስከ 27/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል።በጉባኤ ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ወጣት አመራሮችና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ምሁራን ወጣቶች፣ ወጣት የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ዛሬ ማምሻውን የጅቡቲ፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የኬንያ፣ የአልጄሪያ፣ የብሩንዲ እና የጋቦሮኒ ተወካዮች በጉባኤው ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

 

Please follow and like us: