የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ተሳታፊ ሚኒስትሮች በአዲስአበባ በጎበኙት ነገር መደነቃቸውን ገልፀዋል ።

በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የፓን አፍሪካ ወጣቶች አመራር ጉባኤ ተሳታፊ የወጣት ዘርፍ ሚኒስትሮች አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተርንና የብሔራዊ መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ዋና መሥሪያ ቤትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

ሚኒስትሮቹ በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ አሁንም ለአፍሪካ ስልጣኔ የምታበረክተው አስተዋፅኦ ያላትና በተለያዩ መስኮች እያደረገች ያለችውን ያለውን የስልጣኔ ጉዞ ለሌሎችም ሀገራት ተምሣሌት እንደሚሆን ጠቅሰዋል። አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን ሴንተርንና የብሔራዊ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ም የዚህ አንዱ ምሣሌ መሆኑን ጠቅሰው በጎበኙት ነገርም መደነቃቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ስኬታማ ጉባኤን ለማካሄድ የሚያስችል ዝግጅት ማድረጓን እንደተገነዘቡ ገልፀው አሁንም እንደ አህጉር አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን የሚያረጋግጡ ስራዎችን መስራቷን እንዳዮ ተናግረዋል።

 

Please follow and like us: