Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የሴቶችን የወጣቶች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሰላም ግንባታ ዋና አካልና የአመራር ሚና እንዲኖራቸው እንሠራለን -ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር -ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) “ሰላምን ተለማመዱ በሰላም ኑሩ” የሚል ፕሮጀክት ይፋዊ ማስጀመሪያ ላይ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መ/ቤቱ የሴቶችን የወጣቶች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሰላም ግንባታ ሂደቶች ላይ ከመካተታቸው በዘለል ዋና አካልና የአመራር ሚና እንዲኖራቸው እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ካሉት መጠነ ሰፊ ሃላፊነቶች መካከል አንዱ ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር እና ይህ ትስስር እንዳይጎለብት የሚያደርጉ እንደ ድህነት፣ ግጭት፣ መገለል፣ የእኩልነት አለመኖር እና የአካታች ተሳትፎ እጥረቶችን ለመቅረፍ የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል።እውነተኛ ሰላም ዘላቂ ሊሆን የሚችለው ሁሉም ድምጾች የሚሰሙበት፣ ሁሉም ተሞክሮዎች የሚከበሩበት እና ሁሉም የማህበረሰብ አካላት አስተዋፀኦ ለማድረግ ህጻናት፣ ሴቶች፡ ወጣቶች እና ተጋላጭ የማህበረስብን ክፍሎችን ያካተተ ጠንካራ አገራዊ ሰላምን የመገንባት ስራን በምንሰራበት ወቅት መሆኑ የፕሮጄክቱ ወደ ተግባር መግባት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር አስታውቀዋል።

ፕሮጀክቱ በኤስኦሴስ የህጻናት መንደር፣ ጀርመን የአለም ስነ ህዝብ ፋውንዴሽንና ፒ ኤች ኢ ኢትዮጵያ ጥምረት በአፋር፣ ኦሮሚያና ሶማሊ ክልሎች ለ 3 ዓመት የሚተገበር ሲሆን የገንዘብ ድጋፉ ያደረገው የአውሮፓ ህብረት ነው።
