የመጀመሪያው ምዕራፍ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት መጠናቀቅን ተከትሎ የሚኒስቴር መስሪያቤቱ ስራ አስፈፃሚዎች ጉብኝት አካሄዱ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኔጅመንት አባላት፣ ስራ አስፈፃሚዎች በአሁኑ ወቅት በመልሶ ግንባታ ውስጥ ካሉ ስምንት ዐበይት ኮረደሮች አንዱ የሆነውንና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በይፋ የተመረቀውን የካዛንቺስ አካባቢ ጨምሮ ሌሎች በመጀመሪያው ምዕራፍ የተከናወኑ የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስራዎችን በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቀደም ሲል ይገኝበት የነበረውና በአንድ ወቅት ከተዘነጉ የማዕከላዊ አዲስ አበባ ስፍራዎች አንዱ የሆነው ካዛንቺስን ጨምሮ አካታች እና ተደራሽነቱ የተስፋፋ ሕዝባዊ ስፍራ እንዲሆን በአዲስ ምናብ ተቃኝቶ በዚህ መልክ ማየታቸው ለከተማው አዲስና ውብ ገፅታ ከማላበስ በተጨማሪ ለሴቶች፣ ለወጣቶች፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥና ሰው ተኮር ነው ሲሉ ገልፀዋል።

 

የኮሪደር ስራዎቹ አስፋልት መንገዶችን፣ የእግረኞች መንገዶችን፣ የብስክሌት መንገዶችን፣ የሕፃናት መጫወቻዎችን፣ የስፖርት መሠረተ ልማቶችን፣ የሕዝብ ፕላዛዎችን፣ አረንጓዴ ፓርኮችን፣ የሕዝብ መጸዳጃዎችን፣ ሱቆችን እና የመኪና ማቆሚያዎችን ያካተተ ነው።

Please follow and like us: