Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከል ዛሬ በይፋ ተመረቀ
“በአገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ዜጎቻችን ላይ ምሬት የሚፈጥሩ አሰራሮችን ፈትሾ ማስተካከል ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው። ለዚህ ቁርጠኝነታቸን አንዱ ማሳያ የሆነውን የመሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ማዕከልን ዛሬ መርቀናል።” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ለመሆኑ መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት ምንድን ነው? በማዕከሉ የሚሰጡ አገልግሎቶችስ የትኞቹ ናቸው? ስለሚሉትና ፋይዳውን በተመለከተ በፅሁፉ ተዳሷል። መሶብ የአንድ መስኮት አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የአሰራር ስርዓቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ስራዎችን የሚያስቀር መላ ነው፡፡ አሁን ሥራ ለጀመረው የሙከራ ፕሮጀክት 12 የፌደራል መንግስት ተቋማት የተቀላቀሉ ሲሆን 41 የሚሆኑ የህዝብ አገልግሎቶችንም አቅርበዋል፡፡
እነዚህም ፦
1. የብሄራዊ መታወቂያ አገልግሎት
2. የኢሚግሬሽን እና የዜግነት አገልግሎት
3. የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሌት
4. የገቢዎች ሚኒስቴር
5. የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
6. የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር
7. የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን
8. የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር
9. የትምሀርት ምዘና እና ፍተናዎች አገልግሎት
10. የኢትዮ ፖስታ
11. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
12. ኢትዮ ቴሌኮም ናቸው።
ሀሉም ተቋማት በቴክኖሎጂ አማካኝነት በትስስር አገልግሎት እየሰጡም ይገኛሉ።
ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትከ
