Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር እና የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ወጣቶች የኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
ማህበራቱ የወጣቶች ልማትና ትስስርን ለመፍጠርና ወጣቶች በኢኮኖሚ ዘርፍ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ያለመ ነው። ስምምነቱ በዋናነት በኢኮኖሚና ስራ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ነው።

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ወጣቶች የሚወክል የሃገሪቱ መሪ ተቋም ሲሆን፣ በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ላይ የወጣቶችን አሳተፋ፣ ተሳትፎና እውቅና ለማስፋፋት ይሰራል።በዚህ ስምምነት መሠረት፣ የኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር በኢኮኖሚ ዘርፍ መሪነትን በመውሰድ በወጣቶች ምክርቤት በኩል በተመረጡ የአፈጻጸም እና አዳዲስ ሀሳቦች ላይ ያተኮረ ሥራዎችን ይሠራል።

ስምምነቱ ለወጣቶች የፋይናንስ እውቀት፣ የንግድ ክህሎትና የስራ ፈጠራ እድሎችን ማስፋፋት፤ የወጣቶችን ኢኖቬሽን እና ስራ ፍጠራ ማበረታታት፤ ከፌዴራል እስከ ክልል እና ታችኛው መዋቅር ድረስ ወጣቶችን ማካተት፤ በኢትዮጵያ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች ማህበር በክልል የተመሰረተ አቅምን በወጣት ምክርቤቱ ባለ ማዕከላዊ አገልግሎት እና አጠቃላይ መድረክ ማስተናገድ ማጠናከርን ያካተተ ነው።
Please follow and like us:
