Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ታላቁ ሩጫ ዕድሜ እና ፆታ ሳይለይ ሁሉንም በአንድነትና በአካታችነት የሚያሳትፍ ውድድር መሆኑ ተገለፀ።
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሩጫ ውድድር የተሳታፊዎች ምዝገባ መጀመርንና የ25 ዓመታት ጉዞን ያስቃኘ መርሃ-ግብር አካሂዷል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ዕድሜ እና ፆታ ሳይለይ ሁላችንም በአንድነት የሚታይበት ልዪ ቀን መሆኑን ጠቅሰው በዚህም አካታች በሆነ መልኩ የሚካሄድ ውድድር መሆኑን ጠቅሰዋል።
ከዚህ ቀደምም ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የተለያዪ ኢኒሺቴቮችን በመውሰድና ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል።
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ዘርፍ ተተኪ አትሌቶችን ከማፍራትና ከገፅታ ግንባታ ባሻገር በየጊዜው ከውድድሩ ገቢ በማሰባሰብ ድጋፍ እያደረገና ማህበራዊ ሃላፊነቱንም እየተወጣ በመሆኑ በተጠቃሚዎች ስም አመስግነዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ የቆየውን አጋርነት ከዚህም በኃላ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በየዓመቱ የሚካሔደውና ዘንድሮም ለ25ኛ ጊዜ የሚካሄደው ታላቁ ሩጫ 55ሺህ ተሳታፊዎችን በመያዝ ይካሄዳል ተብሏል።
Please follow and like us:
