Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዙሪያ በትብብር መስራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከኤኢ- ትሬድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጋር ተወያዩ።

ውይይቱ ተቋማቱ በሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ዙሪያ በትብብር መስራት በሚቻልበት ላይ ለመምከር ያለመ ነው። ተቋማቱ የሴቶችና ወጣቶችን አመለካከት በመለወጥ፣ በማነቃቃት፣ በማደራጀት ወደ ንግድ ስራ እንዲገቡ፣ ምርታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ብሎም የፋይናንስና የገበያ ትስስር በመፍጠር የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ በወይይቱ ተገልጿል።
በጋራ መስራቱ የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ችግር ለመፍታት ያስችላልም ተብሏል። በመሆኑም በቀጣይ ተቋማቱ በሴቶችና ወጣቶች የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በተመሳሳይ እየተገበሯቸው ያሉ ፕሮግራሞችን በተሳሰረ መልኩ በትብብር ለመስራት የስራ ሃላፊዎቹ በሰፊው መክረዋል።
Please follow and like us:
