Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሴቶችና ታዳጊ ልጃገረዶችን ለማብቃት የበለጠ አካታች እና ተደራሽ ያደረገ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት ለመገንባት በቅንጅት እንሰራለን – ዶ/ ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
5ኛው ዙር የወጣቶች አመራር ኮንፈረንስና የውድድር መርሀ ግብር የመክፈቻ ስነስርዓት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ማምሻውን ተካሂዷል። የዘንድሮው ኮንፈረንስና የውድድር መርሀ ግብር የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭ እና ከዩኤን ውመን ኢትዮጵጵያ ጋር በመተባበር “ICT and Digital Economy for Girls and Women Empowerment” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አለማችንም ሆነች ሀገራችን ኢትዮጵያ አካታችና ዘላቂነት ያለው ዲጂታል ኢኮኖሚያዊ ለመገንባት ትክረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቀጣይም የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓቱ ሴቶች፣ ታዳጊዎችንና ወጣቶችን አካታችና ተደራሽ ያደረገ እንዲሆን በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
ሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭ እና አጋሮቹ የተሟላ ስብዕና ያላቸው የወደፊት መሪና ዲፕሎማት ወጣቶችን ለማፍራት ላለፉት ተከታታይ አመታት እያከናወኗቸው ላሉ ተግባራት ምስጋና አቅርበዋል። አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
ወጣቶችም ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ለማዳበር፣ ራሳቸውን ለማብቃትና የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በትጋት እንዲሰሩ መክረዋል። ባለድርሻ አካላትም ጥረታቸውን እንዲደግፉ ጠይቀዋል። በተመድ የወጣቶች ሰላም አምባሳደር እና የሴፍ ላይት ኢኒሼቲቭ መስራችና ስራ እስኪያጅ ስለሺ ዑመር በበኩሉ፥ ድርጅቱ ወጣቶች በአመራርነትና ዲፕሎማሲ ዙሪያ በጥልቀት በመወያየት ለችግሮች መፍትሄዎችን እንዲያመላክቱ ለማስቻል እና በዘርፉ ያላቸውን አቅም ለማሳደግ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአምሳለ ውድድር መድረኮችን ሲያዘጋጅ መቆየቱ ተናግረዋል።
በመድረኩ ወጣቶችና የወጣት አደረጃጀቶችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ሌሎችም የሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ተገኝተዋል።
