Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ሚኒስቴሩ ከተባበሩት መንግስታት የሕዝብ ፈንድ ፕሮጀክቶች ትግበራና አፈፃፀም ላይ ተወያየ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒሰትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕዝብ ፈንድ በኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ የሆኑትን ታይዎ ኦሎዩኦሚ ጋር በጋራ የሚመሩ ፕሮጀክቶች ትግበራና አፈፃፀም ዙሪያ ተወያይተዋል ፡፡

ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕዝብ ፈንድ ሚኒስቴሩን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አድንቀው በተለይም ከመሪ የልማት ዕቅዶች ጋር አስተሳሰረው ለመስራትና በተለይም የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት ለመቀየር መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕዝብ ፈንድ በኢትዮጵያ ምክትል ተወካይ የሆኑትን ታይዎ ኦሎዩኦሚ በበኩላቸው በአፋር እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በ2017 -2020 እ.ኤ.አ ተግባራዊ ለማድረግ የታቀደውን በKOICA የሚደገፈውን የልማት ፕሮጀክት ወቅታዊ መረጃ አቅርበዋል።
ፕሮጀክቱ ራስን የማቋቋም አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቶችን ፣ተቋማትን ለማጠናከር አጠቃላይ አካባቢን ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል ።
Please follow and like us:
