‎ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋራ

‎የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሴት አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር ጋር በመሆን ለአካል ጉዳተኛ ሴቶችና ህፃናት ማዕድ የማጋራት መርሐግብር አካሂዷል።

‎ሚኒስቴሩ ለመጪው የትምህርት ዘመን የሚውሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እና ልዩ ልዩ የአካል ድጋፎችን ለአካል ጉዳተኛ ሴቶችና ህፃናት አበርክቷል። በመርሐግብሩ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዳሉት፥ አብሮነትን፣ በጎነትንና ወገናዊ ፍቅርን በሚገልፅ መልኩ በዓልን ማክበሩ ልዩ ስሜት ይፈጥራል ብለዋል። ‎መንግስት አካል ጉዳተኞችን አካታች ያደረገ አሰራር በማጠናከር በሁሉም የህዝብ አገልግሎቶች የእኩል ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
‎
‎በሀገሪቱ በሚካሄዱ የልማት ስራዎች ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እንዲያሳርፉ ልንደግፋቸው ይገባል ብለዋል። ‎ማንም ወደ ኋላ መቅረት የለበትም በሚል የተነደፈው ዘላቂ የልማት ግብ እንዲሳካ ባለድርሻና አጋር አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስቴር ወደፊትም ከማህበሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራና ለአካል ጉደተኞች ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተናግረዋል።

‎አቅመ ደካሞችን የመደገፍ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም መልዕክት አስተላልፈዋል። ማህበሩ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ የሴት አካል ጉዳተኞች ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። ‎ማህበሩ በየዓመቱ የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአካል ጉዳተኞች የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር እንደሚያካሂድ ገልፀው፥ የዘንድሮ አዲስ ዓመት በዓልን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በማክበራችን ደስ ብሎናል ብለዋል።

Please follow and like us: