Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
አካታችና ዘላቂ የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋትና አገልግሎት አሰጣጡን ማቀናጀት ተጋላጭ ዜጎችን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ ወሳኝ እንደሆነ ተገለፀ
”ክህሎቶችን መገንባት፣ ሥራዎችን ማቀላጠፍ፣ ልማትን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ከተካሄደው የ2025 የኢትዮጵያ የሰው ሃብት ልማት ፎረም ጎን ለጎን በማህበራዊ ጥበቃና በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተደርጓል።
በፓናል ውይይቱ የተሳተፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ አካታች የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት መዘርጋትና በየዘርፉ የሚሰጡ የማህበራዊ አገልግሎቶችን ማቀናጀት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንደሀገር በተለያዩ ምክንያቶች ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመደገፍና ተጠቃሚ ለማድረግ በሰፊው እየተሰራና ውጤትም እያስገኘ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ያለውን የማህበራዊ ጥበቃ ስርዓት ማጠናከር ትኩረት የተሰጠው ቀዳሚ ተግባርም መሆኑን ክብርት ሚኒስትሯ ገልፀዋል። የብሔራዊ መታወቂያ ምዝገባ፣ የዲጂታል የክፍያ ስርዓት፣ ወጥ የማህበራዊ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ምዝገባ፣ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ክስተቶችን መቋቋምና ምላሽ መስጠት የሚያስችል ስትራቴጂ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ መንግስት ዘርፉን ለማጠናከርና ዘላቂ እንዲሆን ለማስቻል ያለውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ብለዋል።
ዜጎችን ከተረጂነት ተላቀው ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ እና በሀገራዊ ልማት ላይም የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ለማስቻል የተቀመጠው ሀገራዊ ግብ እንዲሳካም ርብርቡ ተጠናክሮ መቀጠሉንም ተናግረዋል።
የሀገርን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና ለማስቀጠል የሰው ሃብት ልማት ወሳኝ መሆኑን የገለፁት ክብርት ሚኒስትሯ፥ በማህበራዊ ጥበቃ መስክ እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ከአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። ፎረሙ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም ባንክ በጋራ የተዘጋጀው ሲሆን በዋናነት የኢትዮጵያን የሰው ሀብት ልማት ለማሻሻል በሚያስችሉ አዳዲስ ስትራቴጂዎች ዙሪያ ለመምከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።