Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
የክልል እና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የተቋሙን አገልግሎት አሠጣጥ ውጤታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ላይ የስራ ጉብኝት አካሄዱ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ለውጡን ተከትሎ ሁሉን አቀፍ የመንግሥት አገልግሎትና አስተደደር ሪፎርም ተግባራዊ እያደረገችና ውጤትም እያስመዘገበች ትገኛለች።
ሚኒስቴሩም የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻልና ውጤታማ ለማድረግ፣ የአሰራር ባህልን ለመቀየር፣ ጠንካራ ተቋም ለመገንባትና ሪፎርሙን በተሟላ መልኩ ለመተግበር ትኩረት ተሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችም፤ ሚኒስቴሩ ምቹ የስራ ከባቢ በመፍጠር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማጎልበትና ለማዘመን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አስመልክተው ለክልል እና ለከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አስጎብኝተዋል።
ምቹ የስራ ከባቢ መፈጠሩ የስራ ተነሳሽነትን እና ፈጠራን ከማበረታታት ባሻገር ተገልጋዮች ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ በማስቻል እርካታን ለማሳደግ ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
Please follow and like us:
