ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የሀገራችን ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ ዕድገቷ እንዲፋጠንና በአለም አደባባይ ከፍ ብላ እንድትታይ እንደዜጋ በተሰማራንበት መስክ መረባረብ ከሁላችንም ይጠበቃል

‎የሚኒስቴሩ ሰራተኞች 18ኛው ብሔራዊ የሰንድቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
‎‎በመርሃሐግብሩ ላይ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትር አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሰንደቅ ዓላማችን የሉዓላዊነት፣ የአንድነት፣ የአብሮነታችንና የብሔራዊ መግባባት መገለጫ ልዩ አርማ መሆኑን ተናግረዋል። የነፃነታችን ምልክት የሆነው ሰንደቅ ዓላማ ብዙ መስዋዕትነት የተከፈለበትና ለሀገራችንም ያለንን ፍቅር የምናሳይበት በመሆኑ ሁላችንም ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት ይኖርብናል ብለዋል።

 

‎‎ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሠንደቅ ዓላማ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር ታላቅ ሀገራዊ በዓል በመሆኑ በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር መደንገጉን ገልፀዋል። ‎ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የሀገራችን ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ ዕድገቷ እንዲፋጠንና በአለም አደባባይ ከፍ ብላ እንድትታይ እንደዜጋ በተሰማራንበት መስክ መረባረብ ከሁላችንም ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
‎
‎

Please follow and like us: