የቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ

በሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሚመራ የልዑካን ቡድን ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ሚስተር ዌንካይ ዘሄንግ እና የቦርድ አባላት ጋር በኢትዮጵያ የገጠር ልማትን ከማጠናከርና ሴቶችን በግብርና ልማት ረገድ ያላቸውን ሚና ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅትም ክብርት ሚንስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ ውስጥ በገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ ተማሪዎችን በምገባ እና በትምህርት ቁሳቁሶች አቅርቦት የጀመረውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ጠይቀዋል። እንዲሁም የገጠር ሴቶችን በግብርና ልማት ስራ ውጤታማ እዲሆኑ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል።

 

‎የቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ፕሬዝዳንት ሚስተር ዌንካይ ዘሄንግ በበኩላቸው፥ ፋውንዴሽኑ የገጠር የልማት ፕሮጀክቶችን እና ሌሎች የልማት ስራዎችን ማለትም የት/ቤት የተማሪዎች ምገባ እና የተማሪዎች የትምህርት ግብዓት አቅርቦትን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
‎

Please follow and like us: