Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
ግንባታው የቆመን ፕሮጀክት ነፍስ መዝራት መቻል ትልቅ የአመራር ክህሎትና ጥበብ የሚጠይቅ ነው – ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
ግንባታው የቆመን ፕሮጀክት ነፍስ መዝራት መቻል ትልቅ የአመራር ክህሎትና ጥበብ የሚጠይቅ መሆኑን በኮይሻ ፕሮጀክት ታይቷል ሲሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማን አስመልክቶ በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ የተገኙት የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ግንባታው የቆመን ፕሮጀክት ነፍስ መዝራት መቻል ትልቅ የአመራር ክህሎትና ጥበብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል። የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንደ ሀገር የተሻለ ስራ መሰራቱን የሚያሳይና የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የፕሮጀክት ቅልጥፍና ውጤታማነት የታየበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የኮይሻ ግድብን ለሁለተኛ ጊዜ መጎብኘታቸውን በመግለጽም አሁን በተመለከቱት አፈጻጸም መደነቃቸውን ተናግረዋል፡፡ የቆመን ፕሮጀክት ነፍስ መዝራት መቻል ትልቅ የአመራር ክህሎትና ጥበብ የሚጠይቅና መሆኑንና ይህንንም በኮይሻ ፕሮጀክት መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ በተለይም ለግንባታ የሚውሉ ግብዓቶች በአካባቢው ከሚገኙ ሀብቶች የሚገኙ መሆኑ ያላየነው ብዙ ሀብት በእጃችን እንዳለ የሚያሳይ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የአካባቢውን ማህበረሰብ የፕሮጀክቱ ባለቤት ለማድረግ እየተሰሩ የሚገኙ እንደ መንገድና መብራት የመሳሰሉ የማህበራዊ አገልግሎቶች ምሳሌ የሚሆኑ ናቸው ሲሉ ክብርት ሚኒስትሯ አንስተዋል፡፡ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም እንደ ሀገር የተሻለ ስራ መሰራቱን የሚያሳይና የኮይሻ የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጫ የፕሮጀክት ቅልጥፍና ውጤታማነት የታየበት እንደሆነም ገልጸዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።
