Phone: +25111111111 Email: info@mowsa.gov.et
በአማራ ክልል በ2017 ዓ.ም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ656 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸው ተገለፀ።
በአማራ ክልል በ2017 ዓ.ም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ656 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለፁ።
የ2017 ዓ.ም የክረምት ወራት ሀገር አቀፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ እና የዕውቅና መርሐ-ግብር “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሀሳብ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው። በማጠቃለያ መርሐግብሩ በምክትል ርዕሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንዳሉት፥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመንፈስ እርካታ ለማግኘት ሰዎች በፈቃደኝነት የሚሰጡት እና ተግባሩም የሰዎችን ሰብአዊነት የሚያጎለብት አገልግሎት መሆኑን ተናግረዋል።
እንዲሁም የበጎ ፈቃት አገልግሎት ማኅበራዊ መስተጋብርን እያጠናከረ መሆኑን፣ የልማት ክፍተቶችን በመሙላት እና የማኅበረሰቡን መልካም እሴት በማጠናከር ሚናው እየጎላ መምጣቱን ገልጸዋል።
በክልሉ በ2017 ዓ.ም በ14 የስምሪት መስኮች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ከ658 ሺህ በላይ ወጣቶች መሳተፋቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ከ13 ሚሊዮን በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ እንዲሁም ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ የሚሆን የመንግሥትን ወጭም መታደግ መቻሉን ገልጸዋል።።
Please follow and like us:
