የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፬” ለተሳተፉ አካላት የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር አካሄደ።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በ14ቱም የስምሪት መስኮች ለተሳተፉ፣ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ፬” ተሳታፊዎች አካላት የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር አካሄደ።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ መለስ አለሙ በብልፅግና ፓርቲ በሚኒስቴር ማዕረግ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንደገለፁት የዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብርን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከፍተኛ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ጠቅሰዋል። ሚኒስቴር መስሪያቤቱን ጨምሮ በሌሎች የፌደራል ተቋማት በተለያዩ የስምሪት መስኮች ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ጋር በመተባበር አጠቃላይ ሂደቱን በአገር አቀፍ ደረጃ መካሄድ ከፍተኛ የእርስ በርስ ትስስር መፍጠሩን ጠቁመዋል።

በምስጋናና እውቅና ስነ ስርዓቱ ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ፣በሰላም ግንባታ ፣ በትውልድ ግንባታ፣ በጤና፣ ፈጠራ የታከለበት የድጋፍ አሰባሰብ ዘርፍ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራሮችን በመተግበር ፣ በቤት ግንባታ የዘርፍ ተሸላሚዎችን የሸለመ ሲሆን ክልሎች የወጣት አደረጃጀቶች፣ ማህበራት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ምስጋናና እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

Please follow and like us: